ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ የሃባሪ ሜዲካል ፕላዛን መርቀን በይፋ ሥራ አስጀምረናል ብለዋል፡፡
ተቋሙ ለሀገራችን ጥራት ያለው የሕክምና አማራጭ ይዞ የመጣ ማዕከል ነው። ሃባሪ ሜዲካል ፕላዛ ዜጎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚያደርጉትን ጉዞ በማስቀረት፣ ጥራት ያለው አገልግሎት በሀገር ውስጥ ለማቅረብ የጀመረው ጉዞ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመርነው ጉዞ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ ሁሉን አቀፍ ድጋፋችን አይለያችሁም።
ለዚህ በጎ ጅምር እና ለላቀ አገልግሎታችሁ ያለኝን አድናቆት እየገለጽኩ፤ ለተቋሙ ስኬታማ የሥራ ዘመን እመኛለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡