ሀገር በቀል የሆነው አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (ANE) ግብረ ሠናይ ድርጅት፣ የሕይወት አድን ሰብዓዊ እርዳታ እንዲሁም የማገገሚያና የልማት ድጋፍን በማድረስ ረገድ ባከናወነው ሥራ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ተሸለመ።
ድርጅቱ በናይሮቢ በተካሄደው የዓለም ዘላቂነት ምክር ቤት መድረክ ላይ፣ በሚያከናውናቸው ከፍተኛ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ከአፍሪካ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች መካከል ሽልማት ማግኘቱን አስታውቋል።
ይህ እውቅና የተሰጠው ውስብስብ እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የሕይወት አድን ሰብዓዊ ዕርዳታ፣ የማገገሚያ እና የልማት ድጋፍን ለማድረስ ድርጅቱ ባሳየው ቁርጠኝነት ሲሆን ይህም ለሀገር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ተነግሯል።
አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (ANE) ላለፉት 13 ዓመታት በ13 ከተሞች ላይ ተሰማርቶ ስደተኞችን፣ ተፈናቃዮችን እና በተለያዩ ምክንያቶች የተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በምግብ፣ በውሃ፣ በመጠለያ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች እንዲሁም በጤና፣ በትምህርትና በአካባቢ ልማት ዘርፎች ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።
በአቡ ቻሌ