የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን እያረጋገጠ ነው

You are currently viewing የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን እያረጋገጠ ነው
  • Post category:ጤና

AMN ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ2.7 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ከኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ከተማ አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ እንደተገለጸው፣ መርሐ ግብሩ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች የጤና ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ውጤት እንዲገኝ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በወቅቱ እንደገለጹት፣ ከጥቅምት 1 እስከ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነው የነባርና የአዲስ አባላት ምዝገባ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል። ይህም በከተማዋ ፍትሐዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ስራ ስኬታማ አድርጎታል።

በተያያዘም የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከ63 ሚሊዮን በላይ መሻገሩን አስታውቋል። ይህም ኅብረተሰቡ ስለ መድኅን አገልግሎቱ ያለውን ግንዛቤ እያሳደገ መምጣቱን የሚያመለክት መሆኑ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮም ለመርሐ ግብሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ለነበራቸው ባለድርሻ አካላት በዕለቱ ዕውቅና ሰጥቷል።

በቴድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review