ከሜዳው ውጪ በቪታሊቲ ስታዲየም ቦርንማውዝን የገጠመው አርሰናል 3ለ2 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
በጨዋታው ከመጠነኛ ጉዳቱ የተመለሰው አማካዩ ዴክለን ራይስ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ልዩነት ፈጣሪነቱን አሳይቷል።
ለቦርንማውዝ የመጀመሪያ ግብ መቆጠር ስህተት የፈፀመው ጋብርኤል ማጋሌሄስ ሌላኛውን የአርሰናል ግብ አስቆጥሯል።
ለቦርንማውዝ ኤቫኒልሰን እና ጁኒየር ክሩፒ ሁለቱን ግቦች አስገኝተዋል።
አርሰናል ድሉን ተከትሎ ከተከታዩ አስቶንቪላ በስድስት ፣ ነገ ከቼልሲ ጋር ከሚጫወተው ማንችስተር ሲቲ በሰባት ነጥብ እርቆ ሊጉን እየመራ ይገኛል።
በመጨረሻዎቹ 11 የሊግ ጨዋታ አንድም ማሸነፍ ያልቻለው ቦርንማውዝ በአንፃሩ በ23 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አርሰናል በቀጣይ ሳምንት ሊቨርፑልን በኤምሬትስ ያስተናግዳል።
በሸዋንግዛው ግርማ