ዎልቭስ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አገኘ

You are currently viewing ዎልቭስ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አገኘ

AMN ታኅሣሥ 25 ቀን 2018 ዓ.ም

ዎልቭስ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አሳክቷል።

የውድድሩን አጋማሽ ምንም ጨዋታ ሳያሸንፍ ያጠናቀቀው በሦስት ነጥብ ያጠናቀቀው ዎልቭስ ዛሬ በ20ኛ ሳምንት መርሐግብሩ ዌስትሃምን 3ለ0 አሸንፏል።

በሞሌንዩ በተደረገው ጨዋታ ጆን አሪአስ ፣ ህዋንግ ሂ ቻን (በፍጹም ቅጣት ምት) እና ማቴኡስ ማኔ የዎልቭስን የድል ግቦች አስመዝግበዋል።

ድሉ ዎልቭስ ከ20 ጨዋታ ያገኘውን ነጥብ ወደ ስድስት ከፍ አድርጎለታል።

የዛሬን ጨምሮ ከዘጠኝ ተከታታይ ጨዋታ አንድም ማሸነፍ ያልቻለው ዌስትሃም በ14 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ዬገኛል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ብራይተን በርንሌይን 2ለ0 ረቷል።

ግቦቹን ያሲን አያሪ እና ጆርጂኒዮ ሩተር አስቆጥረዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review