የሚኤሶ-ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በቀጠናዊ ትስስር ያላት ሚና የሚያጎለብት ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የሚኤሶ-ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በቀጠናዊ ትስስር ያላት ሚና የሚያጎለብት ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN ታህሳስ 25/2018

የሚኤሶ-ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት የወጪና ገቢ ንግድ የሚያቀላጥፍና ኢትዮጵያ በቀጠናዊ ትስስር ያላትን ሚና የሚያጎለብት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የመንገድ መሠረተ ልማት የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዟችን ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የሚኤሶ – ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት የሚገኝበትን የስራ ሂደት በተመለከተ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

በፕሮጀክቱ የስራ ሂደት እየተከናወኑ የሚገኙ የሰው ኃይል ዝግጅት፣ የማሽነሪና ሌሎች የግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት፣ የመስክ ዝግጅት እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የተደረጉ ውይይቶች ምን ይመስላሉ የሚሉት ጉዳዮች መዳሰሳቸውን አመልክተዋል።

የሚኤሶ – ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ለከባድ የጭነት መኪኖች አዳጋች የነበረውን መንገድ ምቹ በማድረግ፣ የወጪና ገቢ ንግድ እንደሚያቀላጥፍና ኢትዮጵያ በቀጠናዊ ትስስር ረገድ ያላትን ሚና ያጎለብታል ነው ያሉት።

ፕሮጀክቱ የኢኮኖሚውን ተወዳዳሪነትና የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ጉልህ አበርክቶ የሚኖረው በመሆኑ በተያዘለት እቅድ መሠረት እንዲጠናቀቅ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review