በሰራተኞች መካከል የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ምርታማ እና ጤንነቱ የተጠበቀ ሰራተኛ ከማፍራት ባሻገር በአሰሪና ሰራተኛው መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል

You are currently viewing በሰራተኞች መካከል የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ምርታማ እና ጤንነቱ የተጠበቀ ሰራተኛ ከማፍራት ባሻገር በአሰሪና ሰራተኛው መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል

AMN – ታኀሣሥ 26/2018 ዓ/ም

በሰራተኞች መካከል የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ምርታማ እና ጤንነቱ የተጠበቀ ሰራተኛ ከማፍራት ባሻገር በአሰሪና ሰራተኛው መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ገለጸ፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ በየአመቱ የሚያዘጋጀው የ2ዐ18 ዓ/ም የበጋ ወራት የሰራተኞች ውድድር “ስፖርት ለጤንት፣ ለወንድማማችነት እና ለምርታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በውድድሩ መክፈቻ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፤ ስፖርት ለሰራኞች አንድነት ማጠናከሪያ እና ለአሰሪና ሰራተኛ መልካም ግንኙነት አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

እንዲህ አይነት ውድድሮች መዘጋጀታቸው ለሰራተኛው እርስ በእርስ ግንኙነት መጠናከር እንዲሁም ጤናቸውን ለመጠበቅ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተሳታፊ ስፖርተኞች ተናግረው፤ በቀጣይ ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡

ውድድሩ በ10 የተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ ሲሆን፤ ለቀጣይ 6 ወራት የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከ30 ማህበራት የተወጣጡ ከ1,200 በላይ ተወዳሪዎች በውድድሩ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በሰለሞን በቀለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review