“ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለሰላማዊ ምርጫ” በሚል መሪ ሀሳብ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing “ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለሰላማዊ ምርጫ” በሚል መሪ ሀሳብ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

AMN -ታኅሣሥ 26/2018 ዓ.ም

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በመተባበር “ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለሰላማዊ ምርጫ” በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የምክክር መድረኩ በዋናነት በሀገሪቱ እየተገነባ ያለውን የዴሞክራሲ ስርዓት ለማጠናከር እና በቀጣይ የሚካሄዱ ምርጫዎች ከስጋትና ከግጭት የጸዱ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ መድረክ ላይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ተሳታፊዎቹ በጋራ በሚያደርጉት ምክክር ለሀገር ዘላቂ ሰላም የጋራ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት፣ ማንኛውንም የፖለቲካ ልዩነቶች በጠረንጴዛ ዙሪያ በውይይት በመፍታት ቀጣዩን አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲያከናውኑ ቁርጠኝነታቸውን የሚያሳዩበት መድረክ እንደሚሆን ከሠላም ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review