የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ፀሃፊ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

You are currently viewing የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ፀሃፊ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

AMN ታኅሣሥ 26/2018

የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ፀሃፊ ሼክ ካሊፋ ቢን አሊ አል ሃርቲ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፀሃፊዊ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደዋኖ ከድር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሼክ ካሊፋ ቢን አሊ አል ሃርቲ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይገናኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review