ሩበን አሞሪም ተሰናበተ

You are currently viewing ሩበን አሞሪም ተሰናበተ

AMN ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነቱ እንደተሰናበተ ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡

ትናንት ከሊድስ ዩናይትድ ጋር 1ለ1 ከተለያዩ በኋላ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ብቻ ሳይሆን ማናጀር እንደሆነ መናገሩ የክለቡን ሃላፊዎች አላስደሰተም፡፡

ቀደም ብሎም ቅራኔ ውስጥ ገብቷል የተባለው የ41 ዓመቱ አሰልጣኝ ዛሬ ረፋድ ላይ የስንብት ደብዳቤ እንደደረሰው ዘገባው አክሏል፡፡ ክለቡ በአሰልጣኙ ስንብት ዙሪያ ይፋዊ መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review