ሃሳብ የለውጥ ሀይል ነው፣ ምሁራንም የለውጥ ወኪል ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing ሃሳብ የለውጥ ሀይል ነው፣ ምሁራንም የለውጥ ወኪል ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN – ታኀሣሥ 27/2ዐ18 ዓ/ም

ሃሳብ የለውጥ ሀይል ነው፣ ምሁራንም የለውጥ ወኪል ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአልማዝ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓል ማጠቃላያ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ምሁርነት በጊዜና በዘመን ላይ መሰልጠን መሆኑን አብራርተዋል።

መሪነት ለሥልጣኔ ስምረት መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሃሳብ መሪዎች ያለፈውን የሚረዱ መጪውንም ማየት የሚችሉና ዛሬን ጠንክረው የሚሠሩ ናቸው ብለዋል።

ትላንትን መለስ ብሎ ማየት ወደፊት ለመስፈንጠር ያለውን ፋይዳ የማይገነዘቡ ከሆነ ነገን አርቆ ለማየት ይቸገራሉም ብለዋል።

የሃሳብ ምሁር ለመሰኘት፣ትላትን መዳሰስ ዛሬንም ማየት ብቻውን በቂ አይሆንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬን ጠንክሮ መስራት ይጠይቃል ብለዋል።

ሃሳብ የለውጥ ሀይል ነው፣ምሁራንም የለውጥ ወኪል ናቸው ነው፣ሃሳብን ወክለው በተለያዩ ዓውዶች በሰዎች መስተጋብር ውስጥ የሃሳብ ወኪል ሆነው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ውክልናቸውን በወጉ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review