ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ ነው

AMN | ታኅሣሥ 26/2018 ዓ.ም.

ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ በቀጣዮቹ 6 ወራት ለመገንባት እየተዘጋጀች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ዩኒቨርሲቲው ቢያንስ አንድ ሽህ ተመራቂዎችን ለማውጣት የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ለሚመጡ ሁለት ዜጎች በድምሩ ለ100 አፍሪካውያን ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ ታሳቢ ተደርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሳወቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጥናታወ‍ኢ ጽሑፍ ባቀረቡበት ወቅት ነው።

የሚገነባው አዲሱ ዩኒቨርሲቲ የሚቀበላቸው ተማሪዎች በተግባር የተፈተኑና ተጨባጭ ዕውቀት ያላቸው ሲሆኑ ከዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ለሚመጡ ጭምር ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንም እንኳን በትምህርት ክፍል ደረጃ የጀመሩ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ቢኖሩም በዓለማችን ላይ ብቸኛው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ (በአቡዳቢ የሚገኘው የሞሐመድ ቢን ዛይድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ) ብቻ በመሆኑ ኢትዮጵያ ከፈጠነች ሁለተኛዋ ሀገር ትሆናለች ብለዋል።

ትውልድ ላይ መሥራት እሽቅድድም የሚፈልግ በመሆኑ 4ኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ላይ ከምትገኘው ዓለም ጋር ዕኩል መራመድ ብሎም ቀድሞ መገኘት እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳባቸውን ባካፈሉበት መድረክ ላይ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review