ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ/ማን ጎበኙ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ/ማን ጎበኙ

‎AMN ታኅሣሥ 26/2018 ዓ.ም

‎‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር ዛሬ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ጉብኝት ማድረጋቸውን ገለፁ።

‎ጉብኝቱ የሀገራችንን ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ክዋኔ ዐቅም ለመገምገም እና የሀገሪቱን እያደገ ያለ የልማት አጀንዳ ለመደገፍ በሎጂስቲክስ ዝግጁነት ላይ ገንቢ ውይይቶችን ለማካሄድ ጠቃሚ ዕድል ሰጥቶናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።

‎ኢኮኖሚያችን እያደገ ሲሄድ የሎጂስቲክስ ዘርፉ ካልዘመነ ዘላቂ ዕድገትን የሚገድብ ዋና መሰናክል መሆኑን ይቀጥላል ብለዋል።

‎ አሁን በተለይ በውስጣዊ እና በራስ ዐቅም የባቡር መንገድ ግንባታ ላይ የተመዘገበው ዕድገት እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑን አመላክተዋል።

‎ይህም የሀገር ውስጥ ዐቅምን ለመገንባት፣ ውጤታማነትን ለማሻሻል እና በባቡር ዘርፍ ውስጥ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነትን እንደሚሳይ ተናግረዋል።

‎ሎጂስቲክስ ከባሕር እስከ መጋዘኖች ድረስ ያለውን ሙሉ ሰንሰለት እንደሚያካትት ገልጸዋል።

‎ይህም ወደቦች፣ የባቡር መንገዶች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እና የማከማቻ ተቋማትን ይጨምራል ብለዋል።

‎ በአሁኑ ወቅትም በእጃችን ውስጥ ባሉ መስኮች ላይ እንደ ደረቅ ወደቦች፣ የባቡር መሠረተ ልማት፣ አውራ ጎዳናዎች እና የመጋዘን ግንባታ አስፈላጊ ማሻሻያዎችና ዘመናዊ የማድርግ ሥራዎች በሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

‎ እነዚህን ተያያዥ የሎጂስቲክስ ክፍተቶችን በተቀናጀ መንገድ መፍታት የዘርፉን መሰናክሎች ለመሻር እና የሀገሪቱን ሰፊ የልማት ግቦች ለመደገፍ ወሳኝ ይሆናል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review