ማንችስተር ዩናይትድ ቋሚ አሰልጣኝ ለመቅጠር አስከ ክረምት ሊጠብቅ ይችላል

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ ቋሚ አሰልጣኝ ለመቅጠር አስከ ክረምት ሊጠብቅ ይችላል

AMN ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ስንብት ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ረዥም ጊዜ መቆየት እፈልጋለሁ ያለበትን ክለብ ከ14 ወራት በላይ ማሰልጠን አልቻለም፡፡

ክለቡ በአሰልጣኙ ስንብት ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ዳረን ፍሌቸር በጊዜያዊነት ቡድኑን ይረከባል፡፡

ስኮትላንዳዊው አሰልጣኝ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በዋና አሰልጣኝነት የመዝለቅ እድሉ ሰፊ እንደሆነ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡ፍሌቸር ባይሆን እናኳን በውድድሩ መሀል የሚመጣ ሌላ አሰልጣኝ ከጊዜያዊነት ያለፈ ሚና እንደማይሰጠው ተገልጿል፡፡

ማንችስተር ናይትድ በሩበን አሞሪም ላይ የሰራውን ስህተት ላለመድገም ይጥራል ተብሏል፡፡ ክለቡ ኤሪክ ቴንሃግን ካሰናበተ በኋላ ሩበን አሞሪምን ያመጣው ህዳር ወር 2024 ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህም ክለቡ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ ዝቅተኛውን ደረጃ (15ኛ) ይዞ እንዲያጠናቅቅ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል፡፡

ክለቡ ምንም እንኳን ቅጥሩን ክረምት ላይ ያደርጋል ቢባልም አሰልጣኝ ፍለጋውን አሁን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review