በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የአዕላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ

You are currently viewing በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የአዕላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ

AMN | ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.

በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የአዕላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ነገ ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በገና በዓል ዋዜማ በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የዝማሬ መርሐ ግብር በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች በቦታው ተገኝተው የሚከታተሉት ሲሆን ይኸውም መርሐ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ ለመከለከል የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሕዝብ በስፋት ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸው ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እና ብሔራዊ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ኅብረተሰቡ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማበርከቱን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የአዕላፍ ዝማሬ መርሐ ግብርም በሠላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የፕሮግራሙ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

መርሐ ግብሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅም፡-

ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ

ከቦሌ በጌቱ ኮሜርሻል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም ደንበል አካባቢ

ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል የሚወስደው መንገድ በተለምዶ ጋዜቦ አደባባይ

ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ፤ ለቀላል ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ

ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያ መስቀለኛ

ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት

ከአምባሳደር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት

ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግሥት

የሚወስዱ መንገዶች ከታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መርሀ ግብሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ የሚዘጉ ሲሆን ከዛሬ ታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በሚዘጉ መንገዶች ላይ ለረጅም ሆነ ለአጭር ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ኀብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት

በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 በነፃ የስልክ መስመሮች በ987 991 816 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review