የተደመረ ትውልድ መፈጠሩ አይቀሬ ነው

You are currently viewing የተደመረ ትውልድ መፈጠሩ አይቀሬ ነው

AMN- ታኅሣሥ 28/ 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአልማዝ ኢዮቤልዩ (75ኛ ዓመት) የምስረታ በዓል ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠንካራ የውስጥ አንድነት ለመገንባት ተቋማት በጋራ የወል ትርክት ላይ ትኩረት አድርገው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሰዎች አጥራቸውን አፍርሰው በአንድነት መራመድ ከቻሉ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያደገች ሀገር መፍጠር ይቻላል ብለዋል።

ምሁራን ከመንግሥት ጋር በቅርበት መሥራት ይኖርባቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ሲሆን ግንኙነታቸው ከኢንዱስትሪው ጋር እንዲቆራኝ በማድረግ አሁን ላይ የሚታዩትን የእውቀትና የክህሎት ክፍተቶች መሙላት እንደሚቻል ተናግረዋል።

መንግሥት የምሁራንን ሐሳብ ብቻ አድምጦ ፖሊሲ አያደርግም፤ ነገር ግን ነባር የፖሊሲ አቅጣጫዎችን የሚያግዝና የሚያሻሽል ማለፊያ ሐሳብ ከመጣ ለመቀበል ዝግጁ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በቅርቡ በተከናወነው የኮሪደር ልማት ወቅት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኩል የታዩ ውስንነቶች ሊታረሙ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ዓለም አቀፉን የቴክኖሎጂ ማዕበል መቋቋም የሚቻለው በትምህርትና በዕውቀት ብቻ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቴክኖሎጂውን ማቆም ስለማይቻል አብረን ካልተራመድን ወደ ኋላ መቅረታችን አይቀሬ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ደ/ር) በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ የተደመረ ትውልድ እንደሚፈጠር ምንም ጥርጥር የለኝም በማለት ለሀገሪቱ ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review