በገናና የጥምቀት በዓላት ለመታደም የሚመጡ ጎብኝዎች አዳዲስ የመስህብ ሥፍራዎችን የሚጎበኙበት ዕድል ተመቻችቷል

You are currently viewing በገናና የጥምቀት በዓላት ለመታደም የሚመጡ ጎብኝዎች አዳዲስ የመስህብ ሥፍራዎችን የሚጎበኙበት ዕድል ተመቻችቷል

AMN ታኅሣስ 28/2018

በገናና የጥምቀት በዓላት ለመታደም የሚመጡ ጎብኝዎች አዳዲስ የመስህብ ሥፍራዎችን የሚጎበኙበት ዕድል መመቻቸቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታው ስለሺ ግርማ እንደገለጹት፤ የገናና የጥምቀት በዓላት ከእምነቱ ተከታዮች ባሻገር የውጭ ጎብኝዎችን ቀልብ የሚስቡ ታላላቅ ዓመታዊ ክብረ በዓላት ናቸው ብለዋል።

በበዓላቱ ለመታደም የሚመጡ ጎብኚዎች የኢትዮጵያን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችንና የአደባባይ በዓላትን በማስተዋወቅ ለቱሪዝም ዕድገት ወሳኝ ዕድሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በበዓላቱ ለመታደም የሚመጡ ጎብኝዎች የተሻለ የቆይታ እንዲኖራቸው ማድረግ የሚያስችል አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የገናና የጥምቀት በዓላት በድምቀት በሚከበርባቸው አካባቢዎችም ለባለድርሻ አካላት ሥልጠና በመስጠት የቱሪስቶችን የአገልግሎት እርካታ ለመፍጠር ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል።

ከዓለም ክፍሎች በገናና የጥምቀት በዓላት ለመታደም ለሚመጡ ጎብኝዎችም በተለያዩ የመረጃ አማራጮች የበዓላቱን ታሪካዊ ዳራና በድምቀት የሚከበርባቸውን ሥፍራዎች የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት አስጎብኝዎችና ባለድርሻ አካላት አዳዲስ የመስህብ ስፍራዎችን በማስተዋወቅ ጭምር የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ የተሻለ የሚያደርግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በተቀረጹ የጉብኝት ፓኬጆችም በገናና የጥምቀት በዓላትን ለመታደም የሚመጡ ጎብኝዎች አዳዲስ የመስህብ ሥፍራዎችን የሚጎበኙበት ዕድል መመቻቸቱን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም የተሻለ የጉብኝት ምኅዳር ለመፍጠርም አስጎብኝዎች፣ ሆቴሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review