በአዲስ አበባ ደረጃ የሴቶች የአመራርነት ተሳትፎ እድገት ማሳየቱን የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ
ቢሮው ለሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት መጎልበት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ለኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ እንደገለፁት በየደረጃው ባሉ የመንግስት የአመራርነት መዋቅሮች የሴቶች ተሳትፎ በአማካኝ 32 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ሴቶች እስከ ቡድን መሪ ባሉ የአመራርነት ቦታዎች 43 በመቶ ተሳትፎ እንዳላቸው ያመለከቱት ቢሮ ሀላፊዋ፤ በከፍተኛ የአመራር መዋቅሮችም 10 በመቶ አካባቢ የነበረውን ተሳትፎ ወደ 25 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል::
በምክር ቤት ደረጃ የሴቶች ተሳትፎ 50 በመቶ መድረሱን ያስታወቁት ወይዘሮ ቆንጂት፤ በቀጣዩ ምርጫም ይህን ተሳትፎ ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በሽመልስ ታደሰ