የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
“ዘንድሮ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የምናከብረው የተነገረው የተስፋ ቃል መድረሱን፣ የለውጥ ብርሃን መፈንጠቅ መጀመሩን፣ የመሻገር ዘመን መቅረቡን እያመንን ነው።

ጉዟችን በውጣ ውረድ የተሞላ ነበር፤ ተስፋ አስቆራጭ መከራዎችን አስተናግደናል። ከእንግዲህ ፈተናው ጨርሶ አይጎበኘንም ባንልም፣ ተስፋችን የሚወለድበት የዋዜማው ዕለት ላይ ደርሰናል። የፍዳው ዘመን ላይመለስ ተሸኝቶ፣ የማንሠራራት ዘመን እንደመጣ በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን።” ብለዋል፡፡
በዓሉን ስናከብር የፍቅር መገለጫ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስ አርአያ በማድረግ የተቸገሩትን በማሰብ እና በመርዳት ፍቅርን በመግለጥ ይሁን።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት ይሁንላችሁ። በድጋሚ መልካም የልደት በዓል ይሁንልን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡