3ኛው “የአዕላፋት ዝማሬ” በመስቀል አደባባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል

You are currently viewing 3ኛው “የአዕላፋት ዝማሬ” በመስቀል አደባባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል

AMN – ታኅሣሥ 28/2018 ዓ.ም.

በጃንደረባው ትውልድ አጠቃላይ ማኅበር (ኢጃት) አዘጋጅነት ለሦስተኛ ጊዜ የተሰናዳው “የአዕላፋት ዝማሬ” መርሐግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እና በድሬደዋ ለገሀር አደባባይ በታላቅ ድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትና ደንብን በተከተለ መልኩ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማን በምስጋና ለማሳለፍ በማቀድ የተጀመረው መርሐ ግብር ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተገኝተው እያከበሩት ይገኛሉ፡፡

ማኅበሩ የዘንድሮው መርሐግብር በመስቀል አደባባይ እንዲከናወን ምክንያት የሆነውም ባለፉት ሁለት ዙሮች ከተሳተፉ ምዕመናን በተሰበሰበ መረጃ እና በተሠራ የዳሰሳ ጥናት መሠረት የቦታ ጥበትን፣ ከልክ ያለፈ መጨናነቅን ለማስቀረት በማሰብ እና ምዕመናን መርሐግብሩ በመስቀል አደባባይ እንዲከበር በየዓመቱ ያቀርቡት የነበረውን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ማኅበሩ በሰጠው መግለጫ ላይ መግለጹ ይታወቃል።

ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በመሐረነ አብ ጸሎት እና በብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጸሎተ ወንጌል ተጀምሯል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ በአጠቃላይ 30 መዝሙሮች የሚቀርቡ ሲሆን መርሐግብሩ ከምሽቱ 1:30 ላይ እንሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡ መርሐ ግብሩ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና የጸጥታ ቢሮ አስፈላጊውን ትብብር ማድረጉ ይታወቃል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review