ማንችስተር ዩናይትድን መምራት ለእኔ ትልቅ ክብር ነው፦ ዳረን ፍሌቸር

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድን መምራት ለእኔ ትልቅ ክብር ነው፦ ዳረን ፍሌቸር

AMN ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የማንችስተር ዩናይትድ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር ቡድኑን እንዲመራ እድል በማግኘቱ እንደተደሰተ ገልጿል።

የክለቡ የቀድሞ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሩበን አሞሪም ስንብትን ተከትሎ ቡድኑን በጊዜያዊነት ይመራል።

ፍሌቸር ነገ ከብርንሌይ ጋር ከመጫወቱ በፊት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በርካታ ጉዳዮችን አንስቷል።

በተሰጠው እድል እንደተደሰተ ያነሳው ስኮትላንዳዊው አሰልጣኝ “በህልሜም እንኳን አስቤው የማላውቀው” ሲል ያገኘውን እድል ገልፆታል።

በተሰጠው ሚና ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ የተጠየቀው ፍሌቸር ትኩረቱ የበርንሌይ ጨዋታ ብቻ እንደሆነ ተናግሯል።

በረዳትነት ከ21 ዓመት በታች ቡድኑን የሚመሩት እና የክለቡ የቀድሞ ተከላካይ ጆኒ ኢቫንስ አብረውት እንደሚሰሩ ጠቁሟል።

ከተጫዋቾች ጋር በተያያዘ ቡርኖ ፈርናንዴዝ እና ሜሰን ማውንት ከጉዳት አገግመው ወደ ስብስቡ መመለሳቸውን አረጋግጧል።

ቡድኑ እኔ የማውቀው ማንችስተር ዩናይትድን እንዲመስል እፈልጋለሁ ያለው ዳረን ፍሌቸር ሦስት ነጥብ ማግኘት ግን ቀዳሚው ትኩረታቸው እንደሆነ አብራርቷል።

ማንችስተር ዩናይትድ የ21ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብሩን ወደ ተርፍ ሙር በማቅናት ምሽት 5:15 ከበርንሌይ ጋር ያደርጋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review