ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓልን ለማህበራዊ ችግር ከተጋለጡ ወገኖች ፣ የአገር ባለውለታ አረጋውያን፣ አቅመ ደካሞችና ደጋፊ ከሌላቸው ወገኖቻችን ጋር በጉለሌ ‘ተስፋ ብርሃን’ የምገባ ማዕከል ማዕድ በመቋደስ አክብረናል ብለዋል፡፡
እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ከመቀበል ይልቅ በመስጠትና በማካፈል ውስጥ ነው። የከተማችን በረከቶች ከሆኑ ወገኖቻችን ጋር በዓልን ማክበር ለእኛ ታላቅ ክብርና የሞራል ስንቅ ነው። በዛሬው ዕለትም በሁሉም 26ቱ የከተማችን የምገባ ማዕከላት የማዕድ መቋደስ መርሃ ግብር በድምቀት ተካሂዷል ሲሉ ገልጸዋል፡፡