ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓልን ብርሃን የአይነስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ተገኝተን ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙት ከልጆቻችን ጋር መዓድ ተካፍለናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በ2017 ዓ.ም በትምህርት ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎቻችን በሙሉ በማለፋቸው ባመጡት ከፍተኛ ውጤት የተሰማንን ደስታ በመግለጽ የገናን በዓልን ምክንያት በማድረግ የላፕቶፕ ስጦታ አበርክተንላቸዋል ብለዋል፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ ቀንን ስናከብር ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ከሰማይ ሰማያት መውረዱን ለሌሎች መኖርን ያስተማረን መሆኑን በመገንዘብ በፍቅር፣በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ይሁን እያልኩ፡ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆንልን ምኞቴን እገልጻለሁ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡