አዲስ ታለንት ሾው አዲስ አበባ የጥበብ ከተማ እንድትሆን የድርሻዉን እየተወጣ ነዉ ሲሉ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

You are currently viewing አዲስ ታለንት ሾው አዲስ አበባ የጥበብ ከተማ እንድትሆን የድርሻዉን እየተወጣ ነዉ ሲሉ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

AMN – ታኅሣሥ 29/2018 ዓ.ም

አዲስ ታለንት ሾው አዲስ አበባ የጥበብ ከተማ እንድትሆን የድርሻዉን እየተወጣ ነዉ ሲሉ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ላለፉት 13 ወራት ሲከናወን የቆየው የአዲስ ታለንት ሾው የፍፃሜ ውድድር በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተገከናወነ ይገኛል፡፡

በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) አዲስ ታለንት ሾው ትልቅ ተፅእኖ እንደፈጠረ ተናግረዋል፡፡

ቢሮአቸው ኪነጥበብ እንዲያድግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሃላፊዋ በከተማዋ 320 አማተር የኪነ ጥበብ ቡድኖች እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

እነዚህ ቡድኖች ከአማተርነት አልፈው በኢንዱስተሪው ተፅእኖ ፈጣሪ ሆነው እንዲወጡ እንደ አዲስ ታለንት ሾው አይነት ውድድሮች አጋዥ ናቸው ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ኪነ ጥበብ እንዲያድግ በርካታ ተግባራትን እየፈፀመ ነው ያሉት ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለዚህ አጋዥ ሆኖ በመምጣቱ አመስግነዋል፡፡

በሸዋንግዛዉ ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review