ለሕዝብ ቃል የተገቡ የልማት ተግባራትን ለመፈጸም በጊዜ የለኝም መንፈስ መሥራት ይገባል

You are currently viewing ለሕዝብ ቃል የተገቡ የልማት ተግባራትን ለመፈጸም በጊዜ የለኝም መንፈስ መሥራት ይገባል

AMN- ታኀሣሥ 30/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ማካሄድ ጀመረ።

መድረኩ “በሐሳብ፣ በትጋትና በውጤት ወደ ላቀ ሁለተኛ ምዕራፍ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ አመራሩ ለሕዝብ የገባውን የልማት ቃል በተግባር ለመተርጎም ካለው የጊዜ ውስንነት አንጻር በከፍተኛ ትጋትና በጊዜ የለኝም መንፈስ መረባረብ ይኖርበታል።

የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የአመራሩ ሚና ወሳኝ መሆኑንም አሳስበዋል።

አቶ ሞገስ አክለውም በከተማዋ የሚከናወነው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ከአመራሩ የሚጠበቅ ዋነኛ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ዴሞክራሲን በተግባር በማረጋገጥ፣ በመዲናዋ የሚካሄደው የምርጫ ሂደት ለሌሎች ምሳሌ እንዲሆን በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የጽሕፈት ቤት ኃላፊውን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው በዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review