የቻይና አፍሪካ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል

You are currently viewing የቻይና አፍሪካ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል

AMN ታህሳስ 30/2018

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ውይይት አካሄዱ።

ውይይቱ እያደገ የመጣው የቻይና አፍሪካ ትብብርን ማጠናከር ላይ ያለመ ነው ተብሏል።

ቻይና የአፍሪካ እውነተኛ አጋር መሆኗን የገለፁት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው ፖሊሲ ጠንካራ ወዳጅነት እንዲፈጠር ማድረጉን ገልፀዋል።

የቻይና አፍሪካ ግንኙነት በተለያዩ የትብብር ማዕቀፎች እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል።

ከውይይቱ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ ሁለቱ ወገኖች የዓለም ደቡባዊ ቀጣና (Global South) ሀገራትን መብትና ጥቅም ለማስከበር፣ የሉዓላዊነትን ክብር ለመጠበቅ እና ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በጋራ ለመሥራት መስማታቸውን አስታውቀዋል።

በውይይቱ ወቅት የቻይናን የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ከአፍሪካ ኅብረት የ2063 አጀንዳ ሁለተኛው የዐሥር ዓመት ትግበራ ጋር በማጣጣም ዘመናዊነትን ለማምጣት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ምክክር መደረጉ ተገልጿል።

በዚሁ መሠረት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነቶችን ጨምሮ፣ ቻይና ያቀረበቻቸውን ዓለም አቀፍ የደኅንነትና የልማት ተነሳሽነቶች በጋራ ለመደገፍ ከስምምነት መድረሳቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በተጨማሪም የተፈረሙ የትብብር ስምምነቶችን በተግባር በመተርጎም እና የንግድ ልውውጥን በማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት በጋራ መግለጫቸው ማረጋገጣቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review