ባለፉት ስድስት ወራት እንደሀገር በተከናወነ የተቀናጀ ሥራ ከ704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ።
የገቢዎች ሚኒስቴር የ6 ወራት የገቢ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ በስድስት ወራት መሰብሰብ የቻለችው ከ704.4 ቢሊዮን ብር የሚልቅ ገቢ ባለፉት ጊዜያት ለዓመታት ሲሰበሰብ ከነበረው ገቢ የሚስተካከል ነው።
መንግሥት የሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትን የሚደግፉ በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ለተገኘው ውጤት ቁልፍ መነሾ ነው።

አፈጻጸሙ በገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው 640 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ውስጥ 704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 110 በመቶ ማሳካት የተቻለበት ነው።
የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ስድስት ወራት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ63 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን ስኬቱ ኢትዮጵያ የውስጥ አቅሟን በማጎልበት እያንሰራራች ለመሆኑ ሁነኛ ማሳያ ተድርጎ የሚወሰድ ነው።
በግማሽ ዓመቱ ከሀገር ውስጥ ታክስ 362 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ከ341 ነጠብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ተስብስቧል ። ይህም ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን የገቢ አፈጻጸም ያሳየችበት ሀገራዊ ስኬት ነው ። – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት