ስለ ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ምን ያህል ያውቃሉ?

You are currently viewing ስለ ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ምን ያህል ያውቃሉ?

AMN ጥር 02/2018 ዓ.ም

👉 የመጀመሪያው ምዕራፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሥራ በአመት 60 ሚሊዮን ተጓዦችን የማስተናገድ አቅም አለዉ

👉 ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎሜትር አካባቢ በምትገኘውና 1910 ሜትር ከፍታ ባላት ቢሾፍቱ ከተማ ይገነባል

👉 ግንባታዉ ሲጠናቀቅ አፍሪካን ከአለም ቀዳሚ የአየር ትራንስፖርት መነኻሪያዎች አንዷ ያደርጋታል

👉 ሃገሪቱ በአመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ላይ እንድትደርስ ያደርጋል

👉 ቢሾፍቱ ለአውሮፕላኖች ሥራ የተመቸ ከባቢ አላት

👉መዳረሻቸውን ኢትዮጵያ ላደረጉም ሆነ ለትራንዚት መንገደኞች ብቁ ሁኔታ ያላት ከተማ ናት

👉 በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ይሆናል

👉 ከነባሩ የአየር ትራንስፖርት ምኅዳር ጋር በቀላሉ የተዋሃደ አሠራር እንዲኖር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል

👉 ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ 25 ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞችን በአመት የማስተናገድ አቅሙ አለዉ

👉 ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግምባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ አላማን ያነገበ ነው

👉 ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ የኢንደስትሪ ማስፋፊያ አጀንዳ እና የረጅም ዘመን የአቪየሽን ስትራቴጂ ጋር የተናበበ ነው

👉 ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያጠናክራል

👉 በAfCFTA ማህቀፍ የአፍሪካን የማገናኘት አቅም ይጨምራል

👉 የንግድ እና ቱሪዝም ኮሪደሮችን ያሰፋል

👉 ኢትዮጵያንም ቀዳሚ የበይነ አኅጉር ማዕከል ያደርጋታል

#PMOEthiopia

#flytoethiopia

#ethiopianairlines

#linkaddis

#Ethiopia

#addisababa

#aviation

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review