አራዳ ሌግዠሪ ሞል ከአለም አቀፉ አሽሊ ፈርኒቸር ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለዉን የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

You are currently viewing አራዳ ሌግዠሪ ሞል ከአለም አቀፉ አሽሊ ፈርኒቸር ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለዉን የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

AMN ጥር 02/2018 ዓ.ም

አራዳ ሌግዠሪ ሞል ከአለም አቀፉ ግዙፍ የቤት ዕቃዎች አምራች አሽሊ ፈርኒቸር ጋር በይዘቱም ሆነ በአይነቱ የተለየ ሾዉ ሩም ለመክፈት የሚያስችለውን የትብብር ሥምምነት ተፈራርሟል።

አሽሊ ፈርኒቸር በአለም ዙሪያ ከ1ሺህ በላይ ቅርንጫፎች ያሉትና ከ35ሺህ በላይ ሠራተኞችን የሚያስተዳድር በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ፈርኒቸር አምራች ድርጅት ነዉ።

ከተቋሙ ትልቅነት አንጻር ስምምነቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ልዩና ስኬታማ ለአለም አቀፍ ብራንዶች ምርትና አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ዕድልን የሚፈጥር ሲሆን ደረጃዉን የጠበቀ ሃገር አቀፍ እና አለም አቀፍ አገልግሎትን በጋራ ለመስጠት እንደሚያስችል በስምምነቱ ላይ ተገልጿል።

አለም አቀፍ ብራንዶች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገቡ ምቹ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ አለዉ።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀዉ አራዳ ሞል በፒያሳ አድዋ ሙዚየም ፊት ለፊት በመገንባት ላይ ይገኛል።

ሞሉ በ16 ሺህ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ አጠቃላይ የፎቅ ስፋቱ 115 ሺህ ካሬ ሜትር ነው ።

በግንባታው ሂደት እስካሁን ለ1ሺህ 200 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል ።

የህንፃው 48 በመቶ ለውጭ አገር ካምፓኒዎች የሚውል ሲሆን፣ ቀሪው ጥራት ላላቸው የሀገር ውስጥ ድርጅቶች በኪራይ ይተላለፋል።

ሞሉ ዘመናዊና ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶችን በውስጡ የያዘ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ፦

አለም አቀፍ ሱፐር ማርኬቶች እና የፋሽን ብራንዶች: የልጆች መጫወቻ፣ ሲኒማ እና ጂምናዚየም ባንኮች፣ የውጭ ምንዛሪ ማዕከላት እና የቴሌኮም አገልግሎቶች: የአይን እና የጥርስ ሕክምና ክሊኒኮች: ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎች እና የዱዩቲ ፍሪ መሸጫዎች ይገኙበታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review