ከደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀውን የኤሊቶች ወንዶች ውድድር አትሌት ስጦታው ሰማኸኝ አሸንፏል::
አትሌት ቦጋለ በየነ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት አየለ ከበደ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በሴቶቹ ዘርፍ በተደረገ ውድድር አትሌት አማረች ገብሬ ስታሸንፍ አትሌት ደመቅ ጥላሁን እና አትሌት የዘብነሽ ወንዴ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ቋጭተዋል::
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ ከአንኮበር እስከ ሐረር በር በሚል መርሃ ግብር መካሄዱን ቀጥሏል::
በስነ ስርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ በድሉ ውብሸትን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የከተማ አመራሮች ተገኝተዋል:: የልወቅሽ ኢትዮጵያ ውድድሮች በቀጣይ አምስት ከተሞች የሚደረግ ይሆናል።
በታምራት አበራ