ከግብር ከፋይ ጎቦ በመጠየቅ የተቀበለ የኦዲት ባለሙያ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

You are currently viewing ከግብር ከፋይ ጎቦ በመጠየቅ የተቀበለ የኦዲት ባለሙያ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

AMN ጥር 3/2018 ዓ.ም

ከግብር ከፋይ ጎቦ በመጠየቅ የተቀበለ የኦዲት ባለሙያ በቢሮው 7075 ነፃ የስልክ መስመር በደረሰ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ እና የታክስ ኦዲተር ባለሙያ በግብር ከፋይ የቀረበ የወጪ ሰነድ ”አንቀበልም ” በማለት ጉቦ ጠይቀው ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ቢሮው ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ ግብር ከፋዩ ለኦዲት ምርመራ የሚውል ሰነድ አሟልቶ አቅርቦ እያለ ”አላቀረብክም”በሚል የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ጎቦ መጠየቃቸውን ቢሮዉ ገልጿል።

ግብር ከፋዩ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ የያዙ ሰነዶች ማቅረቡን በመግለፅ ”የቀረቡ ሰነዶች እንደ ወጪ አንይዝልህም” በማለት ግብር ከፋዩን ከአንድ ወር በላይ ማመላለሳቸውንም ጨምሮ አሳውቋል፡፡

ሆኖም ግብር ከፋዩ የተጠየቁት ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆን በቢሮው የነፃ የስልክ ቁጥር 7075 አማካይነት ጥቆማ በመስጠታቸው ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ ችለዋል፡፡

በቢሮው በኩልም የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ከፀጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትል ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም የታክስ ኦዲተር ባለሙያው ከተበዳዩ ግብር ከፋይ 50 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙን አሳውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የታክስ ኦዲተር ባለሙያው በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ጎዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል።

የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪዋ ደግሞ በሰራተኞች አስተዳደር ደንብ መሰረት ከኃላፊነቷ እንድትነሳ በማድረግ ጉዳዪ እየተመረመረ መሆኑን ቢሮዉ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review