ማንችስተር ዩናይትድ ከኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ ከኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ

AMN ጥር 3 ቀን 2018 ዓ.ም

ማንችስተር ዩናይት በብራይተን ተሸንፎ ከኤፍ ኤ ካፕ 3ኛ ዙር ውድድር ውጪ ሆኗል።

በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር እየተመራ በኦልድትራፎርድ የተጫወተው ዩናይትድ 2ለ1 ተሸንፏል።

ብሪያን ግሩዳ እና የቀድሞ የዩናይትድ ተጫዋች ዳኒ ዌልቤክ የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።

የዩናይትድን ብቸኛ ግብ ቤንያሚን ሼሽኮ ማስቆጠር ችሏል።

በጨዋታው በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ተቀይሮ የገባው የአካዳሚ ምሩቅ ሼ ሌሲ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ወጥቷል።

ማንችስተር ዩናይትድ በኤፍ ኤ ካፕ 3ኛ ዙር ውጪ ሲሆን በ40 ዓመት ውስጥ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review