ፖሊስን የሚወክል አዲስና ዘመናዊ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በግምገማዉ ላይ እንደገለጹት የፖሊስን የኦፕሬሽን አቅም ለማሳደግ የሚያግዝና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን የሚወክል አዲስና ዘመናዊ የተሽከርካሪ ሠሌዳ በቅርቡ ሥራ ላይ ይዉላል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተቋም የተሰጠው የሊደርሺፕ ቻሌንጅ ሥልጠና የፖሊስ የኦፕሬሽን አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉን እና የሠራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን ኮሚሽነር ጀነራሉ ጨምረዉ ገልፀዋል።