የመንግሥት በጀት ለልጅ ልጅ ለሚሻገር የሀገር ግንባታ እየዋለ ነዉ

You are currently viewing የመንግሥት በጀት ለልጅ ልጅ ለሚሻገር የሀገር ግንባታ እየዋለ ነዉ

AMN AMN- ጥር 04/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመንግሥት በጀት ለልጅ ልጅ ለሚሻገር የሀገር ግንባታ እየዋለ ነዉ ሲሉ ተናገሩ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን አስመልክቶ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ በመንግስት በጀትና በህዝብ ተሳትፎ አመርቂ የልማት ሥራዎች መከናወናቸዉን ገልጸዋል።

በተሰሩት የልማት ሥራዎችም ኢትዮጵያ ደሀ ስለሆነች እንዲህ ዓይነት ግዙፍ ሥራዎችን መሥራት አትችልም የሚለውን የቆየ እሳቤ በተግባር መቀየር መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል።

አንዳንድ አካላት ለመሠረተ ልማት ግንባታ የዋለዉ ይሄ ሁሉ ገንዘብ ከየት መጣ ብለው እንዲጠይቁ ያደረጉት ፕሮጀክቶች የተገነቡት በውጭ ዕርዳታ ሳይሆን በራስ አቅም መሆኑንም ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት በጀት አይሰረቅም ያሉት ከንቲባዋ ይልቁንም ለልጅ ልጅ ለሚሸጋገር የሀገር ግንባታ ልማት እንዲውል እየተደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ባለፈው የበጀት ዓመት ከተመደበው የካፒታል በጀት ውስጥ 71 በመቶ የሚሆነው በቀጥታ ለልማት መዋሉንም ለአብነት አንስተዋል፡፡

ከንቲባዋ አክለውም በአሁኑ ወቅት 1.3 ትሪሊየን ብር ፈሰስ የሚደረግባቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች በመንግሥትና በግል አጋርነት በጋራ እየተገነቡ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

የመዲናዋ ባለሀብቶች በዕውቀታቸውና በገንዘባቸው፣ ማኅበረሰቡም አካባቢውን በማስዋብና ደጀን በመሆን ለውጡን እያገዙ እንደሚገኙ ከንቲባ አዳነች አብራርተዋል፡፡

ይህም በግል ሴክተሩና በመንግስት መካከል ያለውን መተማመን ከፍ አድርጎታል።

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review