የመንገድ ግንባታ በሚከናወንባቸዉቦታዎች ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማትና የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ከቅዱስ ኡራኤል፣ በአትላስ ሆቴል ኤድሞል እስከ ቦሌ ብራስ ድረስ፣ እንዲሁም አደይ አበባ ስታዲየም፣ አካባቢዎች የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ስራው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
በመሆኑም ከጥር 04 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አሳስቧል፡፡