ለሸኔ የሽብር ቡድን እና ለጽንፈኛው ፋኖ ቡድን ሎጂስቲክስ ሲያቀርቡ የነበሩ እንዲሁም ከሽብር ቡድኖቹ ተልዕኮ ወስደው የሰው ሕይወት ያጠፉና አካል ጉዳት ያደረሱ የፀረ-ሰላም ቡድኑን አባላት በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣረባቸው እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

You are currently viewing ለሸኔ የሽብር ቡድን እና ለጽንፈኛው ፋኖ ቡድን ሎጂስቲክስ ሲያቀርቡ የነበሩ እንዲሁም ከሽብር ቡድኖቹ ተልዕኮ ወስደው የሰው ሕይወት ያጠፉና አካል ጉዳት ያደረሱ የፀረ-ሰላም ቡድኑን አባላት በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣረባቸው እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

‎AMN ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዚህ በፊት በሀገራችን ያልተለመዱና የማይታወቁ አዳዲስ የወንጀል ኬዞችን መመርመርና ማጣራት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም ላይ መድረሱን አስታዉቋል፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር የዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ግምገማ ላይ እንደተገለጸዉ ፖሊስ ከዚህ በፊት በሀገሪቱ ያልተለመዱና የማይታወቁ አዳዲስ የወንጀል ኬዞችን መመርመርና ማጣራት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም ላይ ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፈጠረው ከፍተኛ የቴክኖሎጂ አቅም በመጠቀም በኢኮኖሚና ፋይናንስ ወንጀሎች ተሳታፊ የነበሩና የፋይናንስ ተቋማትን የአሠራር ሥርዓትን በማዛባት ከፍተኛ የሀገርና የህዝብ ገንዘብ የመዘበሩ የሀገራችንና የውጭ ሀገር ተጠርጣሪዎችን በረቀቀ የምርመራ ጥበብ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ በግምገማው ላይ ተነስቷል።

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የወንጀል መረብ በመዘርጋት ግለሰቦችን በሐሰት ወደ ተለያዩ ውጪ ሀገራት እንልካችኋለን በማለት በከፍተኛ ደረጃ ወጣቶችን ሲዘርፉና ሲያንገላቱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ተቋሙ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሆነም በግምገማው ላይ ተነስቷል።

ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ ባንክን ተክተው በሕገወጥ የሀዋላ ወንጀሎች ላይ ተሳታፊ የነበሩ እና በኦንላይን የሚያጭበርብሩ ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ታውቋል።

ለሸኔ የሽብር ቡድን እና ለጽንፈኛው ፋኖ ቡድን ሎጂስቲክስ ሲያቀርቡ የነበሩ እንዲሁም ከሽብር ቡድኖቹ ተልዕኮ ወስደው የሰው ሕይወት ያጠፉና አካል ጉዳት ያደረሱ፤ በሀገርና በሕዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ያደረሱ የፀረ-ሰላም ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣረባቸው እንደሚገኝ በግምገማው ላይ ተነስቷል።

በተጨማሪም ከሕዝብና መንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያለአግባብ በመገልገል ከፍተኛ የሙስና ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራባቸው ስለመሆኑ በሪፖርቱ መገለጹን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review