የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር እና ወታደራዊ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ አፋህድ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ከእነ ሠራዊታቸው የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር፣ ወታደራዊ ዋና አዛዥ እና የወሎ ጠቅላይ ግዛት እዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ አፋህድ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር በአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ አማካኝነት ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሰላም ስምምነቱን በመቀበል ከነሠራዊታቸው መግባታቸዉን አሚኮ ዘግቧል፡፡