የወንዝ ዳርቻ ልማት በምናብ ያየናትን አዲስ አበባ በተጨባጭ ቀይረን መሬት ላይ የተገበርንበት የይቻላል ማሳያ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ “በአዲስ አበባ ወንዞች ትንሣኤ” ዘጋቢ ፊልም በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
አዲስ አበባ የስፖርተኞች የአትሌቶች መፍለቂያ እና መኖሪያ ጭምር ናት ያሉት ከንቲባዊ ምንም እንኳን በክልሎች በርካታ አትሌቶች ቢገኙም መኖሪያቸው መለማመጃቸው መሰልጣኛቸው አዲስ አበባ ናት ብለዋል።

በዚህ መነሻነት ለነሱ መታሰቢያ በእንጦጦ አበበ ቢቂላን ከፊት አድርገን ሌሎችን አሰልፈን ማስታወሻ ተሰርተንላቸዋል ብለዋል።
በዚህም ወጣቶች እነሱን እያዩ እንዲነቃቁ ተራራ እንዲወጡና እንዲወርዱ አካላቸውን እንዲያበቁና አዕምሯቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉ የሚያደርግ መሆኑን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገለፁት ::
በሌሎች ሃገራት ትልቅ ተራራ ላይ መውጣት ትልቅ የጉብኝት ማዕከል እና ስፍራ ነው: ይህም በእንጦጦ ላይ ተተግብሯል።
በዚህም አዲስ አበባን ለነዋሪዎቹ ምቹ ለጎብኚዎች ሳቢ አድርገን መልሰን ሰርተን ገንብተናታልም ብለዋል ::
በያለው ጌታነህ