የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ፣ ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳዓር ጋር በኢትዮጵያ እና በእስራኤል መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።
በኢየሩሳሌም በሚካሄደው 4ኛው የኢትዮ-እስራኤል የፖለቲካ ምክክር ዋዜማ ላይ የተካሄደው ይህ ስብሰባ፣ በጋራ ጥቅምና በሁለቱ አገራት ቀጣናዊ እንዲሁም ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዉ አምባሳደር ሀደራ አበራ እና የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳዓር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር የበለጠ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መምከራቸዉንም ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡