በመስሪያ ቤቶች በተከፈቱ የህፃናት ማቆያዎች ከ14 ሺህ በላይ ህፃናት ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing በመስሪያ ቤቶች በተከፈቱ የህፃናት ማቆያዎች ከ14 ሺህ በላይ ህፃናት ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ

AMN- ጥር 5/2018 ዓ.ም

በመስሪያ ቤቶች በተከፈቱ የህፃናት ማቆያዎች ከ14 ሺህ በላይ ህፃናት ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የ ቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በተለይ ለኤኤምኤን ኤፍኤም 96.3 ራዲዮ እንደገለፁት በ970 መንግስታዊ ድርጅቶችና በ15 የግል ድርጅቶች ውስጥ የህፃናት ማቆያዎች መከፈታቸውን ገልጿል ፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪም በዝቅተኛ የኑሮ ድርጃ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የህፃናት ማቆያዎች ፣ የማህበረሰብ አቀፍ የህፃናት ማቆያዎችና የእናቶች የቀን ህፃናት ማቆያዎች መኖራቸውንም የቢሮ ሀላፊዋ አመልክተዋል ፡፡

በእነዚህ የህፃናት ማቆያዎችም ከ14 ሺህ በላይ ህፃናት ተጠቃሚ መሆናቸውን ያመለከቱት ቢሮ ሀላፊዋ ይህም የህፃናቱን ደህንነት በመጠበቅና የሴት ሰራተኞችን ጫና በማቃለል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል ፡፡

በሽመልስ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review