7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጓል

You are currently viewing 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጓል
  • Post category:ፖለቲካ

AMN ጥር 5/2018 ዓ.ም

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡

ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በምክክር መድረኩ ፣ የ7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እና የምክር ቤቶች ሚና ፣ የሕግ ኦዲት እና የፐብሊክ በጀትና ፋይናንስ ትንተና ጥናት ሰነዶች ላይ ምክክር እንደሚደረግባቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ገልጸዋል።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ፣ ሠላማዊና ፍትኅዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ነው አፈ-ጉባኤው ማብራራታቸዉን ምክር ቤቱ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review