ታዋቂው አሜሪካዊዉ ዩቲዩበር እና የቀጥታ ስርጭት አቅራቢዉ ወጣት አይሾው ስፒድ ወይም ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር አዲስ አበባን በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡
በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 21 ቀን 2005 በኦሃዮ አሜሪካ የተወለደዉ ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር በዩቲዩበር ፣ ስትሪመር እና ራፐር ሙያዎቹ በአለም ላይ በስፋት ይታወቃል፡፡
አይሾው ስፒድ በቪዲዮዎቹ ላይ በሚያሳየው ከፍተኛ ጉልበት ፣ ድንገተኛ ጩኸት እና አስቂኝ ድርጊቶች ይታወቃል።
አይሾው ስፒድ በቲክቶክ ላይ በሚለቃቸዉ የራሱ አጫጭር ቪዲዮዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን አግኝቷል።

አይሾው ስፒድ በአሁኑ ወቅት “Speed Does Africa” የተሰኘ ጉዞ እያደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን እየጎበኘ ይገኛል።
በኬንያ በነበረው ቆይታ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ300 ሺህ በላይ አዲስ ተከታዮችን በማግኘት የዩቲዩብ ተከታዮቹን ቁጥር 48 ሚሊዮን አድርሷል።
በኢትዮጵያም በርካታ ዩቱዩበሮች የአዲስ አበባ ጉብኝቱን በመከታተል ላይ ናቸዉ፡፡
ከቅርብ አመታት ወዲህ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ዩቲዩበሮች፤ ቲክቶከሮች፤ ጋዜጠኞች፤ አርቲስቶች፤ የስፖርት ባለሙያዎች፤ የሃገራት መሪዎችና ቱሪስቶች ምርጫቸዉን አዲስ አበባ በማድረግ መዲናዋን ከመጎብኘታቸዉም በላይ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በአለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ