ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ ጋር ተደለደለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ ጋር ተደለደለች

AMN- ጥር 5/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ሳኦቶሜን ይገጥማል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ያደርጋል። የደርሶ መልስ ጨዋታዎቹ በመጋቢት ወር እንደሚከናወን ካፍ አሳውቋል፡፡

የቅድመ ማጣሪያው በፊፋ የሀገራት ደረጃ ዝቅተኛ ቦታ ያላቸው 12 ሀገራት የሚያከናውኑት ነው፡፡ አሸናፊ ስድስት ሀገራት ቀጥታ የምድብ ማጣሪያ ድልድል ውስጥ ይገባሉ፡፡

ኢትዮጵያ ያለፉት ጥቂት ዓመታትን ከዚህ ቅድመ ማጣረያ ርቃ ቀጥታ የምድብ ድልድል ውስጥ ትገባ ነበር፡፡ አሁን ደረጃዋ በመውረዱ ቅድመ ማጣሪያ ውስጥ ለመግባት ተገዳለች፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review