በመዲናዋ የተከናወኑ የወንዝ ዳርቻ የልማት ሥራዎች በመሠረተ ልማት እጦት ተራርቀው የቆዩ ነዋሪዎችን ማገናኘት መቻላቸዉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
በመዲናዋ የተከናወኑ የወንዝ ዳርቻ እና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ሲጎበኙ በሰጡት ማብራሪያ ጉለሌ ላይ ድልድይ ባለመኖሩ ህዝቡ በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ለመገናኘት ሲቸገር መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
የአካባቢው ማኅበረሰብ ብረት እና እንጨት በማስቀመጥ በማይመች ሁኔታ ለመገናኘት ሲሞክር መቆየቱን የገለጹት ከንቲባዋ፣ አሁን ላይ ግን አካባቢውን የማስዋብ ብቻ ሳይሆን የድልድይ ግንባታ በመከናወኑ ሕዝቡን ማገናኘት የሚያስችል ሥራ መሠራቱን አስረድተዋል፡፡
የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቱ እየተከናወነ በሚገኝባቸው አካባቢዎች በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ማመቻቸት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡
በታምራት ቢሻው