የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራና በአቅም ግንባታ ረገድ ዉጤታማ ስራ ማከናወኑን ገለጸ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራና በአቅም ግንባታ ረገድ ዉጤታማ ስራ ማከናወኑን ገለጸ

AMN ጥር 6/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራና በአቅም ግንባታ ረገድ ዉጤታማ ስራ ማከናወኑን የመምሪያው አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማድረግ ጀምሯል።

የመምሪያው አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ባሳለፍነው ጊዜያት በአዲስ አበባ የተከናወኑ ኃይማኖታዊና ሀገራዊ ታላላቅ ኩነቶች በስኬት መከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡

ስኬቱ የተገኘዉ በየደረጃው የሚገኙት አመራርና አባላት ከህብረተሰቡ እና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራታቸዉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራና በአቅም ግንባታ ረገድ ለተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎችም የአመራሩ ሚና የላቀ መሆኑን ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልጸዋል።

በግምገማው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ጨምሮ የጠቅላይ መምሪያው ከፍተኛ አመራሮች ; የአስራ አንዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና የፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች መገኘታቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ያደረሰው መረጃ ጠቁሟል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review