የአበበች ጎበና የሕይወት ጉዞን የሚያስቃኝ ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው

You are currently viewing የአበበች ጎበና የሕይወት ጉዞን የሚያስቃኝ ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው

AMN ጥር 6/2018 ዓ.ም

ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት እና ከ200 በላይ ተዋናያን የተሳተፉበት በአበበች ጎበና ሕይወት ዙሪያ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም ሊመረቅ ነው፡፡

በፊልሙ ምረቃ እንዲሁም ቀጣይ ለሚደረግ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብርን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል ።

የዘጋቢ ፊልሙ ዓላማ ደማቅ የሆነውን የክብርት ዶክተር አበበች ጎበናን የሕይወት ታሪክ ሰንዶ ማቆየት ፤ የሕይወታቸው ሰናይ መርሆዎችና እሴቶችን ለትውልዱ ማስተማሪያ ማድረግ እንደሆነ አቶ እሸቱ አረዶ የአበበች ጎበና ቻሪቲ ዋና ዳይሬክተር በመግለጫው ተናግረዋል።

ከፊልም ምረቃው በተጨማሪ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኘውን የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታልን ለማስፋፋት ለሁለት ወራት የሚቆይ ሀብት የማሰባሰብ ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል ፡፡

የፊልሙ ምረቃና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር “ፍቅር ፣ ርህራሄ ፣ ወደር የማይገኝለት ሰብዓዊነት!’’ በሚል መሪ ሃሳብ ይከናወናል፡፡

አልማዝ ሙሉጌታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review