ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ-ጥር ከሆነው ከኬርፎር (Carrefour) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓትሪክ ላስፋርገስ እና የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ ጋር በከተማዋ ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት በውይይታችን ኬርፎር ከሜድሮክ ኢቨስትመት ግሩፕ ጋር በፈረመዉ ስምምነት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የሚገባበትን ምቹ ሁኔታን በመጠቀም፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የንግድ ትስስሮችን ለማጠናከርና ሌሎችም ታዋቂ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን ወደ ከተማችን ለማምጣት በጋራ ለመሥራት ተግባብተናል ብለዋል።

አዲስ አበባን የኢንቨስትመንትና የንግድ ማዕከል በማድረግ ተወዳዳሪ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።