አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ መሰጠታቸው የንግድ ስርዓቱ የበለጠ ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሆን አስችሏል

You are currently viewing አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ መሰጠታቸው የንግድ ስርዓቱ የበለጠ ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሆን አስችሏል

AMN- ጥር 6/2018 ዓ.ም

የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት እቅዱን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት አፈፃፀሙን የሁሉም ክፍለ ከተሞች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየገመገመ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ ያለፉት ስድስት ወራት ዘመናዊ የንግድ ስርዓትን በመዘርጋትና የገበያ ማዕከላትን እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በማስፋፋት የኑሮ ውድነትን ማቃለል ተችሏል ብለዋል።

አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ ለነጋዴዎች፣ ለአምራቾችና ለሸማቾች በመሰጠታቸው የንግድ ስርዓቱ የበለጠ ቀልጣፋና ተደራሽ እንደሆነም የቢሮ ሀላፊዋ ተናግረዋል።

በመዲናዋ ያለውን የንግድ ሂደት ከብልሹ አሰራር የፀዳ ለማድረግና ፍትሀዊ የሆነ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ባለፉት ስድስት ወራት በየክፍለ ከተሞች በስፋት ስለመሰራቱም ተገልጿል።

ከወረዳዎች፣ ከክፍለ ከተሞች እንዲሁም ከአጎራባች ከተማዎች ጋር የተሰራው የቅንጅት ስራ የንግድ ስርዓቱን ጤናማ እንዲሆን ስለማስቻሉም የክፍለ ከተማ የንግድ ቢሮ ኃላፊዎች በግምገማው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ሥርዓቱን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ፤ አገልግሎትን በማሻሻል የግብይት ሰንሰለትን ማሳጠርና የምርት አቅርቦትን ማሳደግ፤ ገበያን በማረጋጋት ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት እንዲሁም ንግድን ከህገ-ወጥ ድርጊት መከላከል የትኩረት አቅጣጫዎቹ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review