የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያዩ

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያዩ

AMN ጥር 06 /2018

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር በጁባ ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዎን ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከ ልዩ መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ አድርሰዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን ታሪካዊውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

በውይይታቸው የኢኮኖሚ ትብብርን በተለይም የንግድ ፣ኢንቨስትመንት እና ለመሠረተ ልማት ትስስር ቅድሚያ ትኩረት የመስጠትን አስፈላጊነት ገልጸዋል።

የሁለቱን አገራት ሕዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመንገድ እና የኃይል አቅርቦት ትስስርን ትኩረት መስጠታቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review