አዘጋጇ ሞሮኮ ናይጄሪያን አሸንፋ ለፍፃሜ አለፈች

You are currently viewing አዘጋጇ ሞሮኮ ናይጄሪያን አሸንፋ ለፍፃሜ አለፈች

AMN ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም

በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ እና ሞሮኮ ያከናወኑት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በሞሮኮ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ተመጣጣኝ ፉክክር የተደረገበት ጨዋታ በመደበኛው 90 ደቂቃ እንዲሁም በጭማሪው 30 ደቂቃ ግብ አልተቆጠረበትም።

የፍፃሜ ተፋላሚውን ለማወቅ በተሰጠ መለያ ምት ሞሮኮ 4ለ2 አሸንፋለች።

ከ22 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍፃሜ የደረሰችው ሞሮኮ የፊታችን እሁድ ዋንጫውን ለማንሳት ከሴኔጋል ጋር ትጫወታለች።

ተሸናፊዋ ናይጄሪያ 3ኛ ደረጃን ለማግኘት ግብፅን ትገጥማለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review